4 ኤሊሁ፣ ሌሎቹ በዕድሜ ይበልጡት ስለ ነበር ከእነርሱ ቀድሞ ለኢዮብ ሳይናገር ቈየ።
5 ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ።
6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤“እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ፈርቼ ዝም አልሁ።
7 ‘ዕድሜ ይናገራል፤ረጅም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር።
8 ነገር ግን በሰው ያለው መንፈስ፣ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ፣ማስተዋልን ይሰጣል።
9 ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም፤የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም።
10 “ስለዚህ፣ ‘ስሙኝ፣እኔም የማውቀውን ልንገራችሁ’ እላለሁ።