ኢዮብ
ምዕራፎች 32:6-12
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
6ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤“እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ፈርቼ ዝም አልሁ።
7‘ዕድሜ ይናገራል፤ረጅም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር።
8ነገር ግን በሰው ያለው መንፈስ፣ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ፣ማስተዋልን ይሰጣል።
9ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም፤የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም።
10“ስለዚህ፣ ‘ስሙኝ፣እኔም የማውቀውን ልንገራችሁ’ እላለሁ።
11እናንተ በምትነጋገሩበት ጊዜ ታገሥሁ፤ቃላት እየመረጣችሁ ስትናገሩ፣በጥሞና ሰማኋችሁ፤
12በሙሉ ልብ አዳመጥኋችሁ፤ነገር ግን ከእናንተ የኢዮብን ቃል ያስተባበለ ማንም የለም፤ለንግግሩም አጸፋ የመለሰ አልተገኘም።