ዘሌዋውያን 5:13-19 NASV

13 ሰውየው ከእነዚህ በአንዱ ኀጢአት ቢሠራ፣ ካህኑ በዚህ ሁኔታ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። ከመሥዋዕቱ የተረፈውም እንደ እህል ቊርባን ሁሉ ለካህኑ ይሆናል።’ ”

14 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

15 “ማንኛውም ሰው በደል ቢፈጽም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከተቀደሰ ከማናቸውም ነገር በማጒደል ኀጢአት ቢሠራ፣ ከመንጋው እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቅርብ። የዋጋውም ግምት በቤተ መቅደሱ ሰቅል መሠረት ተመዝኖ በጥሬ ብር ይሁን፤ ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።

16 ከተቀደሱ ነገሮች ያጐደለውንም ይተካ፤ የዚህንም ተመን አንድ አምስተኛ በላዩ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም ከበጉ ጋር የበደል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።

17 “ ‘ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዛት ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል።

18 እርሱም ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት የሚሆን እንከን የሌለበት አውራ በግ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ ይሁን። ካህኑም በዚህ ሁኔታ ሰውየው ሳያውቅ ስለ ፈጸመው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።

19 ይህ የበደል መሥዋዕት ነው። ሰውየውም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ጥፋት በመፈጸሙ በደለኛ ነው።”