ዘኁልቍ 13:18-24 NASV

18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ።

19 የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ?

20 ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልባ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ ፍሬ ይዛችሁ ኑ። ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።

21 ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ።

22 በኔጌብ በኩል አልፈው አኪመን፣ ሴሲና ተላሚ የተባሉ የዔናቅ ዝርያዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን መጡ። ኬብሮን የተመሠረተችው ጣኔዎስ በግብፅ ምድር ከመቈርቈሯ ሰባት ዓመት አስቀድሞ ነበር።

23 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንንም ከሮማንና ከበለስ ጋር በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።

24 እስራኤላውያን የወይን ዘለላ ስለ ቈረጡባትም ያች ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተባለች።