18 ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል።
19 በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ሕፃን ልጅ እንኳ ቈጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል።
20 በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፣ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፣ከእንግዲህ ወዲህበመታቸው ላይ አይታመኑም፤ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ፣በእውነት ይታመናሉ።
21 የተረፉት ይመለሳሉ፣ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።
22 እስራኤል ሆይ፤ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፣የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ።ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።
23 ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል።
24 ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤“በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ግብፅ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው።