4 ለድኻ መጠጊያ፣በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ከማዕበል መሸሸጊያ፣ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል።የጨካኞች እስትንፋስ፣ከግድግዳ ጋር እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
5 እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው።የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።
6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
7 በዚህም ተራራ ላይ፣በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
8 ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።ጌታ እግዚአብሔርከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤የሕዝቡንም ውርደትከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
9 በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤“እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤በእርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
10 የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋር እንደሚረገጥ፣ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።