14 ስለዚህ ይህን ሕዝብ በድንቅ ላይ ድንቅነገር እያደረግሁ፣ዳግመኛ አስገርመዋለሁ፤የጥበበኞች ጥበብ ይጠፋል፤የአስተዋዮችም ማስተዋል ይበናል።”
15 ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ለሚወርዱሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣“ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው!
16 እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ፤ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣“እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን?ሸክላ የሠራውን፣“እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?
17 ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን?
18 በዚያን ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤የዐይነ ስውሩም ዐይኖችከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።
19 ትሑታን በእግዚአብሔር፣ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ።
20 ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ፌዘኞችም በነው ይጠፋሉ፤ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።