12 ክብር ለእግዚአብሔር ይስጡ፤ምስጋናውንም በደሴቶች ያውጁ።
13 እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።
14 “ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።
15 ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ኵሬውን አደርቃለሁ።
16 ዕውሮችን በማያወቁት መንገድእመራቸዋለሁ፤ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ።ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ።ይህን አደርጋለሁ፤አልተዋቸውም።
17 በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።
18 “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።