ኢሳይያስ 65:3-9 NASV

3 በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤

4 በመቃብር መካከል የሚቀመጡ፣በስውር ቦታዎች የሚያድሩ፣የዕሪያ ሥጋ የሚበሉ፣ማሰሮዎቻቸውን በረከሰ ሥጋ መረቅ የሚሞሉ ናቸው፤

5 ‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ’ የሚሉ ናቸው።እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።

6 “እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጦአል፤ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤

7 የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ”ይላል እግዚአብሔር።“በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣በሰፈሩት ቊና ይሰፈርባቸዋል፤ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ሰዎችም፣ ‘በውስጡ ጥሩ ነገር ስላለአትቊረጡት’ እንደሚሉ፣እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።

9 ከያዕቆብ ዘር የሆኑትን፣ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሱትን አመጣለሁ።የተመረጠው ሕዝቤ ይወርሳቸዋል፤ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።