21 የተረፉት ይመለሳሉ፣ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።
22 እስራኤል ሆይ፤ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፣የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ።ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።
23 ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል።
24 ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤“በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ግብፅ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው።
25 በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”
26 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደመታ፣በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤በግብፅ እንዳደረገውም ሁሉ፣በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።
27 በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ከውፍረትህም የተነሣቀንበሩ ይሰበራል።