31 ማድሜናህ በሽሽት ላይ ነች፤የጌቢም ሕዝብ ሊደበቅ ይሮጣል።
32 በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻነቀነቁ።
33 እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በታላቅ ኀይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ረጃጅም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።
34 ጥቅጥቅ ያለውን ደን በመጥረቢያ ይቈራርጣል፤ሊባኖስም በኀያሉ ፊት ይወድቃል።