1 ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።
2 የእግዚአብሔር መንፈስ፣የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኀይል መንፈስ፣የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።
4 ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5 ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሰባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።