1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ንግር፤
2 በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፣በእጅ ምልክት ስጡ።
3 በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።
4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣የሚሰማውን ጩኸት አድምጡበመንግሥታትም መካከል፣እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ!የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።
5 እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።
6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።
7 ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።