11 ዓለምን ስለ ክፋቷ፣ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤የጨካኞችንም ጒራ አዋርዳለሁ።
12 ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፣ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።
13 ስለዚህ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ቍጣው በሚነድበት ቀን፣ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ።
14 እንደሚታደን ሚዳቋ፣እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፣እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።
15 የተማረከ ሁሉ ይወጋል፤የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።
16 ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ።
17 እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፣ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ።