16 ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ።
17 እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፣ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ።
18 ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ሕፃናትን አይምሩም፤ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።
19 የመንግሥታት ዕንቍ፣የከለዳውያን ትምክሕት፣የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።
20 በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤የሚቀመጥባትም የለምዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።
21 ነገር ግን የምድረ በዳ አራዊት በዚያ ይተኛሉ፤ቀበሮዎች ቤቶቿን ይሞላሉ፤ጒጒቶች በዚያ ይኖራሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም ይዛለሉበታል።