1 ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች።የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።
2 ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ራስ ሁሉ ተመድምዶአል፤ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል።
3 በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤በየሰገነቱና በየአደባባዩሁሉም ያለቅሳሉ፤እንባም ይራጫሉ።
4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ድምፃቸው እስከ ያሀድ ድረስ ተሰማ፤ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ልባቸውም ራደ።