1 ከምድረ በዳው ማዶ ካለችው ከሴላ፣ለምድሪቱ ገዥ፣ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራየበግ ጠቦት ግብር ላኩ።
2 ከጐጆአቸው ተባርረውግራ እንደ ተጋቡ ወፎች፣የሞዓብ ሴቶችምበአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ።
3 “ምክር ለግሱን፤ውሳኔ ስጡን፤በቀትር ጥላችሁንእንደ ሌሊት አጥሉብን፤የሸሹትን ደብቁ፤ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።
4 የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋር ይቈዩ፤እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።”የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ጥፋቱ ያከትማል፤እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።