6 መስኖዎቹ ይከረፋሉ፤የግብፅ ጅረቶች ይጐድላሉ፤ ይጠፋሉም።ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል፤
7 እንዲሁም በዐባይ ዳር፣በወንዙ መፋሰሻ ላይ ያሉት ተክሎች ይጠወልጋሉ።በዐባይ ዳር የተዘራው ዕርሻ ሁሉ፣በነፋስ ይወሰዳል፤ ምንም አይቀርም።
8 ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ጒልበታቸው ይዝላል።
9 የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ።
10 ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል።
11 የጣኔዎስ አለቆች በጣም ሞኞች ናቸው፤የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ”እንዴት ትሉታላችሁ?
12 የእናንተ ጠቢባን አሁን የት አሉ?የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበግብፅ ላይ ያሰበውን ነገር፣እስቲ ያሳዩአችሁ፤ ያሳውቋችሁም።