1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤
2 በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።
3 ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤በጐዳናውም እንሄዳለን።”ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
4 እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል።እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።