ኢሳይያስ 2:2-8 NASV

2 በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።

3 ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤በጐዳናውም እንሄዳለን።”ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።

4 እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል።እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።

5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።

6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን፣ሕዝብህን ትተሃል፤እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ከባዕዳን ጋር አገና ይማታሉ።

7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ሀብታቸውም ልክ የለውም።ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።

8 ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።