1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ፤ጢሮስ ተደምስሳለችና፤ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች።ከቆጵሮስ ምድር፣ዜናው ወጥቶላቸዋል።
2 እናንት የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣በደሴቲቱ የምትኖሩ፣የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ።
3 በታላላቅ ውሆች ላይ፣ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤የዐባይ መከር ገቢዋ ነበር፤እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።
4 አንቺ ሲዶና ሆይ፣አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፣ ዕፈሪ፤ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሎአልና።
5 ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።
6 እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤