18 ከሽብር ድምፅ የሚሸሽ፣ወደ ጒድጓድ ይገባል፤ከጒድጓድ የወጣም፣በወጥመድ ይያዛል።የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፤የምድርም መሠረት ተናወጠ።
19 ምድር ተከፈለች፤ምድር ተሰነጠቀች፤ምድር ፈጽማ ተናወጠች።
20 ምድር እንደ ሰካራም ዞረባት፤ነፋስ እንደሚወዘውዘውም ጐጆ ሆነች፣የዐመጿ ሸክም ከባድ ስለ ሆነ ትወድቃለች፤እንደ ገናም አትነሣም።
21 በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣በላይ በሰማያት ያሉትን ኀይሎች፣በታችም በምድር ያሉትን ነገሥታት ይቀጣቸዋል።
22 በጒድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል፣ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ።
23 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣በሽማግሌዎቹም ፊት በክብሩ ይነግሣል፤ጨረቃ ትሸማቀቃለች፤ ፀሓይም ታፍራለች።