2 ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ተመልሳም አትሠራም።
3 ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።
4 ለድኻ መጠጊያ፣በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ከማዕበል መሸሸጊያ፣ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል።የጨካኞች እስትንፋስ፣ከግድግዳ ጋር እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
5 እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው።የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።
6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
7 በዚህም ተራራ ላይ፣በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
8 ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።ጌታ እግዚአብሔርከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤የሕዝቡንም ውርደትከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።