21 እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
22 እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።
23 አድምጡ ድምፄን ስሙ፤አስተውሉ ቃሌንም ስሙ።
24 ገበሬ ሊዘራ መሬቱን ሲያዘጋጅ ያለ ማቋረጥ ያርሳልን?ጓሉን ሲከሰክስ፣ ዐፈሩን ሲያለሰልስ ይከርማልን?
25 ዕርሻውን አስተካክሎ፣ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን?ስንዴውንስ በትልሙ፣ገብሱን በተገቢ ቦታው፣አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን?
26 አምላኩ ያስተምረዋል፤ትክክለኛውንም መንገድ ያሳየዋል።
27 ጥቍር አዝሙድ በመውቂያ መሣሪያ አይወቃም፤ከሙን የሠረገላ መንኰራኵር አይሄድበትም፤ጥቍር አዝሙድ በበትር፣ከሙንም በዘንግ ይወቃል።