4 በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋትወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።
5 በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ለተረፈው ሕዝቡ፣የክብር ዘውድ፣የውበትም አክሊል ይሆናል።
6 እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣የፍትሕ መንፈስ፣ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣የኀይል ምንጭ ይሆናል።
7 እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገደገዱ፤በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።
8 የማእድ ገበታቸው ሁሉ በትፋት ተሞልቶአል፤ከትውኪያም የጸዳ ቦታ የለም።
9 እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው?መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው?ወተት ለተዉት ሕፃናት?ወይስጡት ለጣሉት?
10 በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይትእዛዝ፤በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት ነውና።