1 “ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው”ይላል እግዚአብሔር፤“የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ።
2 እኔን ሳይጠይቁ፣ወደ ግብፅ ይወርዳሉ፤የፈርዖንን ከለላ፣የግብፅንም ጥላ ለመጠጊያነት ይፈልጋሉ።
3 ነገር ግን የፈርዖን ከለላ ውርደት ይሆንባችኋል፤የግብፅም ጥላ ኀፍረት ያመጣባችኋል።
4 ምንም እንኳ ሹሞች በጣኔዎስ ቢኖሯቸውም፣መልእክተኞቻቸው ሓኔስ ቢደርሱም፣