30 እግዚአብሔር በሚነድ ቍጣና በሚባላ እሳት፣በወጀብና በነጐድጓድ፣ በበረዶም ድንጋይ፣ግርማ የተሞላበትን ድምፁን ሰዎች እንዲሰሙ አድርጎ ያሰማል፤ክንዱም ስትወርድ ያሳያቸዋል።
31 የእግዚአብሔር ድምፅ አሦርን ያስደነግጣል፤በትሩም ይመታቸዋል።
32 እግዚአብሔር የሚያወርድባቸው የቅጣትበትር ሁሉ፣በከበሮና በበገና ድምፅ የታጀበ ነው፤በጦርነትም ክንዱን አሳይቶ መታቸው።
33 ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያስፍራ ተዘጋጅቶአል፤ለንጉሡም ተበጅቶአል፤ማንደጃ ጒድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስእንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።