ኢሳይያስ 30:4-10 NASV

4 ምንም እንኳ ሹሞች በጣኔዎስ ቢኖሯቸውም፣መልእክተኞቻቸው ሓኔስ ቢደርሱም፣

5 ውርደትና ኀፍረት ብቻ እንጂርዳታም ሆነ ረብ በማያስገኙላቸውምንም ጥቅም በማይሰጧቸው ሰዎች ምክንያትሁሉም ለኀፍረት ይዳረጋሉ።”

6 በኔጌቭ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ተባዕትና እንስት አንበሶች፣መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣

7 ርዳታዋም ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ወደ ሆነው ወደ ግብፅ ይሄዳሉ።ስለዚህ ስሟን፣ረዓብ፣ ምንም የማትጠቅም ብዬ እጠራታለሁ።

8 አሁንም ሂድ፤ በሰሌዳ ላይ ጻፍላቸው፤በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ክተብላቸው፤ለሚመጡትም ዘመናት፣ለዘላለም ምስክር ይሆናል፤

9 እነዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ፣ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው።

10 ባለ ራእዮችን፣“ከእንግዲህ ራእይን አትዩ” ይላሉ፤ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤“እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ደስ የሚያሰኘውን ንገሩን፤የሚያማልለውን ተንብዩልን።