6 በኔጌቭ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ተባዕትና እንስት አንበሶች፣መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣
7 ርዳታዋም ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ወደ ሆነው ወደ ግብፅ ይሄዳሉ።ስለዚህ ስሟን፣ረዓብ፣ ምንም የማትጠቅም ብዬ እጠራታለሁ።
8 አሁንም ሂድ፤ በሰሌዳ ላይ ጻፍላቸው፤በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ክተብላቸው፤ለሚመጡትም ዘመናት፣ለዘላለም ምስክር ይሆናል፤
9 እነዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ፣ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው።
10 ባለ ራእዮችን፣“ከእንግዲህ ራእይን አትዩ” ይላሉ፤ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤“እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ደስ የሚያሰኘውን ንገሩን፤የሚያማልለውን ተንብዩልን።
11 ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ፤ከጐዳናውም ራቁ፤ከእስራኤል ቅዱስ ጋርፊት ለፊት አታጋጥሙን።”
12 ስለዚህ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፤“ይህን ቃል ስላቃለላችሁ፣ግፍን ስለታመናችሁ፣ማታለልን ስለ ተደገፋችሁ፣