9 እነዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ፣ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው።
10 ባለ ራእዮችን፣“ከእንግዲህ ራእይን አትዩ” ይላሉ፤ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤“እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ደስ የሚያሰኘውን ንገሩን፤የሚያማልለውን ተንብዩልን።
11 ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ፤ከጐዳናውም ራቁ፤ከእስራኤል ቅዱስ ጋርፊት ለፊት አታጋጥሙን።”
12 ስለዚህ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፤“ይህን ቃል ስላቃለላችሁ፣ግፍን ስለታመናችሁ፣ማታለልን ስለ ተደገፋችሁ፣
13 ስለዚህ ይህ ኀጢአት፣ተሰነጣጥቆ ሊወድቅ እንደ ደረሰ፣ሳይታሰብ ድንገት እንደሚወድቅ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።
14 ከስብርባሪዎቹም መካከል፣ለፍም መጫሪያ፣ለውሃ መጥለቂያ ገል እስከማይገኝ ድረስ፣ምንም ሳይቀር ክፉኛ እንደሚንኰታኰት፣የሸክላ ዕቃ ይደቃል።”
15 የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም፤