1 እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።
2 እያንዳንዱ ሰው ከነፋስ መከለያ፣ከወጀብም መጠጊያ ይሆናል።በበረሓም እንደ ውሃ ምንጭ፣በተጠማም ምድር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።
3 የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።
4 የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤አጥርቶም ይናገራል።
5 ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ጋጠወጥም አይከበርም።