3 የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።
4 የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤አጥርቶም ይናገራል።
5 ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ጋጠወጥም አይከበርም።
6 ሰነፍ ስንፍናን ይናገራል፤አእምሮው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበትን አድራጐት ይፈጽማል፤ በእግዚአብሔርም ላይ የስሕተት ቃል ይናገራል፤ለተራበ ምግብ ይከለክላል፤ለተጠማ ውሃ አይሰጥም።
7 የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ክፋት ያውጠነጥናል።
8 ጨዋ ግን ሐሳቡም ጨዋ ነው፤በጨዋነት ምግባርም ጸንቶ ይገኛል።
9 እናንት ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች፣ተነሡ፤ ድምፄን ስሙ፤እናንት ተደላድላችሁ የምትኖሩ፣ ሴቶች ልጆች ሆይ፤የምነግራችሁን አድምጡ።