1 በዚያን ቀን ሰባት ሴቶችአንዱን ወንድ ይዘው፣“የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።
2 በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።
3 በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።
4 ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።