18 እንግዲህ፣ እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ?ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?
19 የተቀረጸውንማ ምስል ባለጅ ይቀርጸዋል፤ወርቅ አንጥረኛም በወርቅ ይለብጠዋል፤የብር ሰንሰለትም ያበጅለታል።
20 እንዲህ ያለውን መባ ማቅረብ የማይችል ምስኪን ድኻ፣የማይነቅዝ ዕንጨት ይመርጣል፤የማይወድቅ ምስልን ለማቆምም፣ታዋቂ ባለ ሙያ ይፈልጋል።
21 አላወቃችሁምን?አልሰማችሁምን?ከጥንት አልተነገራችሁምን?ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
22 እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው።ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።
23 አለቆችን ኢምንት፣የዚህን ዓለም ገዦች እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል።
24 ተተክለው ምንም ያህል ሳይቈዩ፣ተዘርተው ምንም ያህል ሳይሰነብቱ፣ገና ሥር መስደድ ሳይጀምሩአነፈሰባቸው፤ እነርሱም ደረቁ፤ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ወሰዳቸው።