ኢሳይያስ 40:20-26 NASV

20 እንዲህ ያለውን መባ ማቅረብ የማይችል ምስኪን ድኻ፣የማይነቅዝ ዕንጨት ይመርጣል፤የማይወድቅ ምስልን ለማቆምም፣ታዋቂ ባለ ሙያ ይፈልጋል።

21 አላወቃችሁምን?አልሰማችሁምን?ከጥንት አልተነገራችሁምን?ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?

22 እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው።ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።

23 አለቆችን ኢምንት፣የዚህን ዓለም ገዦች እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል።

24 ተተክለው ምንም ያህል ሳይቈዩ፣ተዘርተው ምንም ያህል ሳይሰነብቱ፣ገና ሥር መስደድ ሳይጀምሩአነፈሰባቸው፤ እነርሱም ደረቁ፤ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ወሰዳቸው።

25 ቅዱሱ፣ “ከማን ጋር ታወዳድሩኛላችሁ?የሚስተካከለኝስ ማን አለ?” ይላል።

26 ዐይናችሁን አንሡ፤ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤እነዚህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው?የከዋክብትን ሰራዊት አንድ በአንድ የሚያወጣቸው፣በየስማቸው የሚጠራቸው እርሱ ነው።ከኀይሉ ታላቅነትና ከችሎታው ብርታት የተነሣ፣አንዳቸውም አይጠፉም።