13 እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።
14 “ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።
15 ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ኵሬውን አደርቃለሁ።
16 ዕውሮችን በማያወቁት መንገድእመራቸዋለሁ፤ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ።ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ።ይህን አደርጋለሁ፤አልተዋቸውም።
17 በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።
18 “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።
19 አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ?ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ?ለእኔ ታማኝ እንደሆነ ሰው የታወረ፣እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው?