17 በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።
18 “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።
19 አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ?ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ?ለእኔ ታማኝ እንደሆነ ሰው የታወረ፣እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው?
20 ብዙ ነገርን አያችሁ፤ ነገር ግን አላስተዋላችሁም፤ጆሮአችሁ ክፍት ነው፤ ነገር ግን ምንም አትሰሙም።”
21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሲል፣ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስአለው።
22 ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣በጒድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ተበዝብዘዋል፣የሚያድናቸውም የለም፤ተማርከዋል፣“መልሷቸው” የሚልም የለም።
23 ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው?