21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሲል፣ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስአለው።
22 ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣በጒድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ተበዝብዘዋል፣የሚያድናቸውም የለም፤ተማርከዋል፣“መልሷቸው” የሚልም የለም።
23 ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው?
24 ያዕቆብን ለዝርፊያ፣እስራኤልን ለምርኮ የዳረገ ማነው?በኀጢአት የበደልነው፣ እግዚአብሔር አይደለምን?መንገዱን ለመከተል፣ለሕጉም መታዘዝ አልፈለጉምና።
25 ስለዚህ የሚነድ ቍጣውን፣የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።