3 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ግብፅን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።
4 ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣እኔም ስለምወድህ፣ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።
5 ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
6 ሰሜንን፣ ‘አምጣ’፣ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣
7 በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”
8 ዐይን እያላቸው የታወሩትን፣ጆሮ እያላቸው የደነቈሩትን አውጣ።
9 ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ሰውም ይከማች፤ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው?ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ።