1 “ነገር ግን አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣የመረጥሁህ እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤
2 የፈጠረህ፣ በማሕፀን የሠራህ፣የሚረዳህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ባሪያዬ ያዕቆብ፣የመረጥሁህ ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።
3 በተጠማ ምድር ላይ ውሃ፤በደረቅ መሬት ላይ ወንዞችን አፈሳለሁና፤መንፈሴን በዘርህ፣በረከቴንም በልጅ ልጅህ ላይ አወርዳለሁ።
4 እነርሱም በለመለመ መስክ ላይ እንደ ሣር፣በወንዝ ዳር እንደ አኻያ ዛፍ ይበቅላሉ።
5 አንዱ፣ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ሌላው ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራልሌላው ደግሞ በእጁ ላይ ‘የእግዚአብሔር ነኝ’ ብሎ ይጽፋል፤ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።