22 “እናንት የምድር ዳርቻ ሁሉ፣እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።
23 ጒልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ብዬ በራሴ ምያለሁ፤የማይታጠፍ ቃል፣ከአፌ በጽድቅ ወጥቶአል።
24 ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።”በእርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።
25 ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ሞገስንም ያገኛሉ።