ኢሳይያስ 45:4-10 NASV

4 ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣በስምህ ጠርቼሃለሁ፤የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።

5 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ከእኔ በቀር አምላክ የለም።አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣እኔ አበረታሃለሁ።

6 ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣እስከ መጥለቂያው፣ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።

7 እኔ ብርሃንን ሠራሁ፤ ጨለማንም ፈጠርሁ፤አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’

8 “እናንት ሰማያት፣ ጽድቅን ከላይ አዝንቡ፤ደመናትም ወደ ታች አንጠብጥቡ፤ምድር ትከፈት፤ድነት ይብቀል፤ጽድቅም አብሮት ይደግ፤እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።

9 “ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ከሠሪው ጋር ክርክር ለሚገጥም ወዮለት፤ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን?የምትሠራውስ ሥራ፣‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?

10 አባቱን፣‘የወለድኸው ምንድን ነው?’ ለሚል፣እናቱንም፣‘ምን ወለድሽ’? ለሚል ወዮለት።