ኢሳይያስ 48:2-8 NASV

2 እናንት የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪዎች ነን ብላችሁ ራሳችሁን የምትጠሩ፣በእስራኤል አምላክ የምትታመኑ፣ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው የሚለውን አድምጡ፤

3 የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤እኔም ድንገት ሠራሁ እነርሱም፤ ተፈጸሙ።

4 የቱን ያህል እልኸኛ እንደ ነበርህ ዐውቃለሁና፤የዐንገትህ ጅማት ብረት፣ግንባርህም ናስ ነበር።

5 ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኖአል’እንዳትል ነው።

6 እነዚህን ነገሮች ሰምተሃል፤ ሁሉንም ተመልከታቸው፤ራስህ ትክክለኛነታቸውን አትመሰክርምን?“ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣የተሰወሩብህን ያላወቅሃቸውን ነገሮች እነግርሃለሁ።

7 እነርሱም የተፈጠሩት አሁን እንጂ ጥንት አይደለም፤ስለ እነርሱም ከዛሬ በፊት አልሰማህም።ስለዚህ፣ ‘አዎን፤ ስለ እነርሱ ዐውቃለሁ’ማለት አትችልም።

8 አልሰማህም ወይም አላውቅህም፤ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።