8 አልሰማህም ወይም አላውቅህም፤ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።
9 ስለ ስሜ ስል ቍጣዬን አዘገያለሁ፤ስለ ምስጋናዬም ስል ከአንተ እገታዋለሁ፤ይኸውም እንዳልቈርጥህ ነው።
10 እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።
11 ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ?ክብሬን ለማንም አልሰጥም።
12 “ያዕቆብ ሆይ፤የጠራሁህ እስራኤል ሆይ፤ ስማኝ፤እኔ እኔው ነኝ፤ፊተኛው እኔ ነኝ፤ ኋለኛውም እኔ ነኝ።
13 ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤በምጠራቸው ጊዜ፣ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ።
14 “ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።