ኢሳይያስ 5:1-7 NASV

1 ስለ ወዳጄ፣ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይየወይን ቦታ ነበረው።

2 መሬቱን ቈፈረ፤ ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት።በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤የወይን መጭመቂያ ጒድጓድም አበጀ፤ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።

3 “እናንት በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስቲ ፍረዱ።

4 ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምንሊደረግለት ይገባ ነበር?መልካም የወይን ፍሬ ያፈራል ብዬስጠብቅ ለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?

5 እንግዲህ በወይኔ ቦታምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፤ዐጥሩን እነቅላለሁ፤ለጥፋት ይጋለጣል፤ግንቡንም አፈርሳለሁ፣መረጋገጫም ይሆናል።

6 የማይኰተኰትና የማይታረምጠፍ መሬት አደርገዋለሁ፤ኵርንችትና እሾኽም ይበቅልበታል፤ዝናብም እንዳይዘንብበትደመናዎችን አዝዛለሁ።”

7 የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርየወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤የይሁዳ ሰዎችምየደስታው አትክልት ናቸው።ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።