8 ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤ታዲያ ማን ሊከሰኝ ይችላል?እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም!ተቃዋሚዬስ ማን ነው?እስቲ ይምጣ!
9 የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤የሚፈርድብኝስ ማን ነው?እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ብልም ይበላቸዋል።
10 ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው?ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤በአምላኩም ይደገፍ።
11 አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ።እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤በሥቃይም ትጋደማላችሁ።