ኢሳይያስ 51:14-20 NASV

14 ዐንገታቸውን የደፉ እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤በታሰሩበትም ጒድጓድ ውስጥ አይሞቱም፤እንጀራ አያጡም።

15 ሞገዱ እንዲተም ባሕሩን የማናውጥ፣እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

16 ቃሌን በአፍህ አኖርሁ፤በእጄ ጥላ ጋረድሁህ፤ሰማያትን በስፍራቸው ያስቀመጥሁ፣ምድርን የመሠረትሁ፣ጽዮንንም፣ ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ ያልሁ እኔ ነኝ።

17 ከእግዚአብሔር እጅ፣የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ተነሺ፤ ተነሺ።

18 ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣የመራት አንድም አልነበረም፤ካሳደገቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም አልነበረም።

19 እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ታዲያ ማን ያጽናናሻል?እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽኀሀ

20 ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቊጣ፣የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።