ኢሳይያስ 51:16-22 NASV

16 ቃሌን በአፍህ አኖርሁ፤በእጄ ጥላ ጋረድሁህ፤ሰማያትን በስፍራቸው ያስቀመጥሁ፣ምድርን የመሠረትሁ፣ጽዮንንም፣ ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ ያልሁ እኔ ነኝ።

17 ከእግዚአብሔር እጅ፣የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ተነሺ፤ ተነሺ።

18 ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣የመራት አንድም አልነበረም፤ካሳደገቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም አልነበረም።

19 እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ታዲያ ማን ያጽናናሻል?እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽኀሀ

20 ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቊጣ፣የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።

21 ስለዚህ አንቺ የተጐዳሽ፣ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ ይህን ስሚ።

22 ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ ከእጅሽ፣ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ያንን ጽዋ፣ የቊጣዬን ዋንጫ፣ዳግም አትጠጪውም፤