ኢሳይያስ 53:2-8 NASV

2 በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።

3 በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር።ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።

4 በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ሕመማችንንም ተሸከመ፤እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።

5 ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ስለ በደላችንም ደቀቀ፤በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6 እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደልበእርሱ ላይ ጫነው።

7 ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣አፉን አልከፈተም።

8 በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ከትውልዱ ማን አስተዋለ?