ኢሳይያስ 53:4-10 NASV

4 በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ሕመማችንንም ተሸከመ፤እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።

5 ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ስለ በደላችንም ደቀቀ፤በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6 እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደልበእርሱ ላይ ጫነው።

7 ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣አፉን አልከፈተም።

8 በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

9 በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣አሟሟቱ ከክፉዎች፣መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ።

10 መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።